ኑሮ በናሽቭል እና ኦወን ላይፍ (Ethiopia)


ሒወት በአሜካ እና ሒወት በኢትዮፒያ እጅግ የተለየ ነው። መጀመሪያ ወደ ናሽቭል ስመጣ ብዙ ያልጠበኩት ነገሮች ነበሩ; ለመሳሌ ቤት መፈለግ፤ የትራንስፖርት ሁኔታ እና ግሮሰሪ መግዛት። ግሮሰሪ በምገዛበት ጊዜ አንድ የለመድኩት እቃ ማግኘት ከባድ ነው እናም ሁለት ለአንድ እቃ አይነት ብዙ አማራጭ አላቸው። የአማራጭ ብዛት እስከ ዛሬ እንደ ሸወደኝ ነው። ሌላ ያልጠበኩት ደገሞ የሰው ደግነት ነው። በጣም ቸርና አሳቢ ናቸው። ሰውን ለማገዝ በጣም ይጥራሉ። ናሽቭል ከተማ “ምዩዚክ ሲቲ” በመባል ይታወቃል። ይህም ሰበብ በካንትሪ ሙዚቃ ታዋቂ ስለሆነ ነው እናም ብዙ የካንትሪ ዘፋኝ አፍርተዋል። በዚህም ተጨማሪ ከተማው በታም ያምራል። በደቡብ ስቴት ቢገኝም ያደገ እና በደንብ እየበለጸገ ያለ ከተማ ነው። በተጨማሪ ናሽቭል የተለያዩ መስህቦች አሊት፣ ፓርቴኖን፤ ብርጅስቶን አሪና፤ ብሮድዌ፤ ኦፕሪላንድ እና ሌሎች። ስለናሽቭል ሌላ ድስ የሚል ነገር የአየር ሁኔታው ነው። አራት የአመት ወቅቶች አሉት፣ ሆኖም ግን ወቅቶቹ መካከለኛ ናቸው፣ በታምም አይበርድም በታምም አይሞቅም።

ኦወን ግራጁዌት ስኩል ኦፍ ማኔጅመንት የቫንደርብልት ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የብዝነስ ትምህርት ቤት ነው። በአሜሪካ 25ኛ የብዝነስ ትምህርት ቤት ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞች አሊት። ኦወን ግራጁዌት ስኩል ኦፍ ማኔጅመንት የቫንደርብልት ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የብዝነስ ትምህርት ቤት ነው። በአሜሪካ 25ኛ የብዝነስ ትምህርት ቤት ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞች አሊት። የትምህርት አሰጣጣቸው ከኢትዮፒያ እጅግ ይለያል። ይክፍል ተሳትፎ በጣም ብዙ ቱክረት ይሰጠዋል ሆኖም የመጨረሻ ውጤት በፈተና ሳይሆን በተግባር ስራ ነው። ይህም ተግባር ስራ የሚያተኩረው ፔፐር በመጻፍና ፕረዘንቴሽን በመስጠት ነው። ኦወን ከሌላው ብዝለስ ትምህርት ቤቶች የሚለይብት አንድ ባለው ይተማሪ ቁጥር ሲሆን ይህም ሲነጻጸር ያነሰ ነው። ቢሆንም ግን ይህ ከተማሪ መካከል ያለውን ግኑኝነት ያጠናክራል። በተጭማሪ ከተማሪና ከአስተማሪ መካከል ያለውን ግኑኝነትም የተሻለ ይሆናል። የኔ ክላስሜቶች በብዛት አሜሪካዊ ቢሆኑም ሌሎች ከተለያዩ አህጉራት የመጡም አሉ፣ እነዚም ከህንድ፤ ሜክሲኮ፤ ፔሩ፤ ኮሎምቢያ፤ ቻይና፤ ስዊትዘርላንድ፤ ዝምባብዌ እና ሌሎች ናቸው። ከትምህርት ውጪ በዙ የተለያዩ አክትቪቲዎችም አሉ፣ ለምሳሌ የተማሪ ክበቦች። እንኚም እንደ ፋይናንስና ኦፐሬሽንዝ፣ እንደ ላቲን እና ኢንዲያን ክበብ፣ እንዲሁም እንደ ሶሻል አክቲሺቲዝ ክበብ ናቸው።

 

Tags: Africa, Amharic, Ethiopia, international

Comments & Responses

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share this Page